ስለ ኩፍኞች (Amharic)

ኩፍኝ በከፍተኛ መጠን የሚተላለፍ እና ትኩሳት፣ ሽፍታ፣ ሳል፣ እና የዓይን መቅላት እና እንባን የሚያስከትል ከባድ በሽታ ነው።በዋነኛነት የሚተላለፈው በአየር ኩፍኝ የያዘው ሰው ሲያስል ወይም ሲያስነጥስ ነው። 

child with measlesየኩፍኝ ምልክቶች መታየት የሚጀምሩት ተጋላጭ ከሆነ ከሰባት እስከ 21 ቀናት ነው። ኩፍኝ ሽፍታው ከመታየቱ በግምት አራት ቀን በፊት ጀምሮ ሽፍታው ከጠፋ በኋላ እስከ አራት ቀን ድረስ ተላላፊ ነው። ሰዎች የኩፍኝ ምልክት የሆነው ሽፍታ ሳይወጣባቸው በፊት የኩፍኝ በሽታውን ሊያስተላልፉ ይችላሉ። 

ያልተከተቡ ሰዎች፣ ነፍሰጡር ሴቶች፣ ከስድስት ወር በታች የሆኑ ጨቅላ ህጻናቶች እና አነስተኛ በሽታ የመከላከል አቅም ያላቸው ሰዎች ለኩፍኝ በሽታ በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ ናቸው። አንድ ሰው የሚከተሉት ካሉ የኩፍኝ በሽታ የመከላከል አቅም እንዳለው ይቆጠራል፣ 

  • የተወለዱት ከ1957 በፊት ነው
  • የኩፍኝ በሽታን የመከላከል አቅም እንዳሎት የሚያሳይ የደም ምርመራ ውጤት አሎት 
  • ከዚህ በፊት ኩፍኝ ይዞት እንደሚያውቅ በሀኪም የተረጋገጠ መሆኑን እርግጠኛ ከሆኑ 
  • የኩፍኝ ክትባቶችን በወቅቱ የሚወስዱ ከሆነ (እድሜያቸው 12 ወራት እስከ ሶስት ዓመት ለሆናቸው ልጆች አንድ ዶዝ፣ አራት ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ለማንኛውም ሰው ሁለት ዶዞች)።

የሚከተለው ሰንጠረዥ በአካባቢው ያለውን የኩፍኝ ጉዳዮች ሪፖርቶችን ያሳያል

ዓመት
የስኖሆሚሽ ካውንቲ
ዋሺንግተን ስቴት
201703
201868
2019190
202001
20210--


measles flyer doh amharicአልፎ አልፎ የሚከሰቱ ጉዳዮች እና አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ጉዳዮች የሚያጋጥሙት አብዛኛውን ጊዜ ኩፍኝ በብዛት ወደላበት አገር ተጉዘው በሚመጡ ሰዎች ነው። ትላልቅ ወረርሽኞችም የሚከሰቱት አብዛኛውን ጊዜ በተመሳሳይ መንገድ ነው ነገር ግን የሚስፋፋው ቫይረሱ አነስተኛ የክትባት ሽፋን ያለው አካባቢ ውስጥ ከገባ ነው። ባለ 2 ዶዝ የኩፍኝ ክትባት አስተማማኝ እና በጣም ውጤታማ እና ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ክትባት ቢሆንም እንኳን፣ ሙሉ በሙሉ የተከተቡ ግለሶቦችም ቢሆኑ አልፎ አልፎ ኩፍኝ ሊይዛቸው ይችላል። በ2019 ወረርሽኝ ወቅት፣ ከተያዙት ሰዎች ውስጥ 4% ብቻ ሙሉ በሙሉ የተከተቡ ሰዎች ናቸው። 

የክትባት መረጃ

ወላጆች እና አሳዳጊዎች https://wa.myir.net፣ ጋር በመግባት ወይም የህክምና አቅራቢያቸውን በማነጋገር የልጃቸውን የክትባት ሁኔታ ማረጋገጥ እና የክትባት ሰርተፊኬቱን ፕሪንት ማድረግ ይችላሉ። 

ክትባቶች እድሜያቸው እስከ 18 ለሆኑ ልጆች ያለምንም ክፍያዎች ይሰጣሉ። የጤና እንክብካቤ አቅራቢ ክትባቱን ለመስጠት ክፍያ ካስከፈለ፣ ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች አቅማቸው ካልቻለ ክፍያው ቀሪ እንዲደረግላቸው መጠየቅ ይችላሉ። በህግ፣ ማንኛውም ልጅ በመደበኛው የጤና እንክብካቤ አቅራቢው ቤተሰቡ መክፍል ስላልቻለ ክትባት ከማግኘት ሊከለከል አይችልም።